በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ምዝገባ እየተካሄደ ነው


አዲስ አበባ መጋቢት 08/2014(ኦርጂን) በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ በሳምንታዊ መግለጫቸው በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲና በሌሎች ዋና ዋና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ እስካሁን 35 ሺህ ዜጎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

የምዝገባ ሂደቱ መቀጠሉን ጠቁመው ተገቢውን ማጣራት እየተደረገ በቅርቡ ወደ አገር ቤት የሚመለሱ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ደህንነት ለማስጠበቅም ከአገሪቱ የደህንነት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል ብለዋል።

አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው የኢትዮ-ቻይናን ወዳጅነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ገንቢ ምክክር መካሄዱን አክለዋል።

በተያዘው ሳምንትም አዳዲስ አምባሳደሮች ወደ ጃፓን፣ አሜሪካ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ ኩባ፣ ኤርትራ፣ እና ሌሎች አገራትም የሥራ ስምሪት መደረጉንም ጠቅሰዋል።

ይህን ተጭነው ቴሌግራም ግጻችን ይከተሉን ፤


Post a Comment

አዲስ የድሮ