ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ስኬታማነት የመገናኛ ብዙኃን የላቀ ሚና ይጠበቅባቸዋል



መጋቢት 8 2014(ኦርጂን) ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ስኬታማነት የመገናኛ ብዙኃን የላቀ ሚና የሚጠበቅባቸው መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።

የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የሚዲያና የኮሙኒኬሽን የምክክር መድረክ “እውነተኛ መረጃ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፤ መገናኛ ብዙኃን ለአገር አንድነት፣ የሰላም ግንባታና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የላቀ ሚና እንዳላቸው አስገንዝበዋል።

መገናኛ ብዙኃኑ በተለይም በኢትዮጵያ ለተጀመረው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ስኬታማነት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

አገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግስት ዘርፉን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ መገናኛ ብዙኃኑ ለአገር ሁለንተናዊ ግንባታ ሂደት የላቀ ሥራ ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በበኩላቸው፤ መገናኛ ብዙኃን ለአገራዊ ለውጡ መሳካት እንዲሁም ለህግ ማስከበር ሂደቱ የነበራቸውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አንስተዋል።

በቀጣይም ለአገር ሁለንተናዊ ግንባታ፣ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እንዲሁም ለአገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የተጠናከረ ሥራ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።


የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ  እንዳሉት፤ መገናኛ ብዙኃን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጓቸው መረጃዎች አብሮነትና መተማመንን የሚያጎለብቱ እንዲሆኑ መሥራት አለባቸው።

የዘርፉ ባለሙያዎች ዘገባዎቻቸው ከሞራል እና የሙያ ስነ-ምግባር አንጻር የተቃኙ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በመድረኩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይቱ የሚቀጥል ይሆናል።

Post a Comment

አዲስ የድሮ