ፀሐፊ ፡ ቃላብ ግርማ ፤
ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ አዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ
ኤምባሲ መግቢያ በር አካባቢ በርካታ ኢትዮጲያውያን ሩሲያ ከዩክሬን በሚያደርጉት ጦርነት ላይ ከሩሲያ ወገን ተሳታፊ ለመሆን ለመመዝገብ
ወረፋ ላይ ናቸው በሚል የተጠፈው ምስል እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ጉዳዩን በ አዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በቃል አቀባዩ በኩል
ኢትዮጲያውያን ለ ሩሲያ በ ኢሜል እንዲሁም በአካል ከ ሩሲያ ጎን መሆናቸውን እያሳወቁ መሆናቸውን ተናግረው ሩሲያ ለዩክሬኑ ጦርነት
ኢትዮጲያውያንን ለመቅጠር ማስጣወቂያ እንዳላወጡ ና በማህበራዊ ትስር ገፆች የሚናፈሰው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ብሏል፡፡
በአንዳንድ ከቦታው መረጃ ደረሰን ከሚሉ ሰዎች እንዲሁም የዜና ምንጮች
የሚሰሙ መረጃዎች ግን ይህ ሁሉ የአዲስ አባባ ነዋሪ በ ሩሲያ ኤምባሲ በር ላይ መሰብሰቡ ለ ድጋፍ ሳይሆን ለ ምዝገባ እንደገሆነ
ይናገራሉ የሩሲያ ኤምባሲም ምዝገባ እያከናወነ ስላለመሆኑ እንጂ ብዙ ቁጥር ያለው ኢትዮጲያዊ ወጣት እና ጎልማሳ በምን ምክንያት
በበሩ ላይ ሊሰበሰቡ እንደቻሉ ከመናገር ተቆጥቧል፡፡
ኢትዮጲያ ካለችበት የኑሮ ደረጃ አኳያ ወጣቱ ለመዝመት ቢሰለፍ የሚያስገርም
አይደለም በአንድ ወቅት የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት እንዲህ ወር ሳያስቆጥር እንፋሎቱ ሳይበርድ አንድ ናይጄሪያዊ ወጣት በናይጄሪያ
ከምኖር ለሩሲያ ብዋጋ ይሻለኛል ማለቱ ሲያነጋግረ ቆይቶ ነበር ፡፡ ይህ ናይጄሪያዊ ለሩሲያ እንዲዋጋ ካስቀመጠው ቅድም ሁኔታዎች
መካከል ሩሲያ ጣርነቱን ስታሸንፍ የመኖሪያ ፍቃድ የማግኘቱን ጉዳይ ነው፡፡
ታዲያ በሀገራችን ምን ያህሉ ማህበረሰብ ውጪ ሄዶ የቤተሰቡን እንዲሁም
የራሱን ህይወት ለመለወጥ ያቅዳል መልሱ በሁላችንም ዘንድ ያለ እና የማያሻማ ነው ፡፡ ማሳያ ካስፈለገም አሜሪካ እንደ ኢትዮጲያ
ላሉ ሀገራት ባዘጋጀችው የዲቪ ፕሮግራም ተሳታፊ ለመሆን ምንያህል ኢትዮጲያውያን በየአመቱ እንደሚመዘገቡ መመልከት በቂ ነው፡፡ እርግጥ
ነው የ ሩሲያ ኤምባሲውን ሰልፍ ለየት ያደረገው ሪስክ አልያም አደጋው የሰፋ በመሆኑ ነው፡፡ ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን በየአመቱ
ስንት ኢትዮጲያውያን በ ህገወጥ መንገድ ከሀገር ለመሰደድ ይሞክራሉ የሚለው ነው በተለያየ ግዜ እንደሰማነው በባህር እንዲሁም በበረሃ
ሀገር ለማቋረጥ የሚደረግ ጉዞ ከጦርነት የከፋ አደጋ ነው ያለው ምክንያቱም
ህይወትን በእግዜር እጅ ጥሎ እጅን አጣጥፎ የሚደረግ ጉዞ ነው ጦርነት እንኳን በ ትንሹም ቢሆን እራስ መከላከያ አማራጭን ይቸራል፡፡
ከባህር እንዲሁም ከበረሀው የተረፈው ስደተኛ ደግሞ በሳወዲ እስር ቤቶች ሲማቅቁ አይተናል ከዚም አልፎ በሊብያ በረሀ በአይ ኤስ የሽብር ቡድን በአሰቃቂ ሁኔታ ነብሳቸውን ያጡ ኢትዮጲያውያንን
ማስታወስ በቂ ነው ፡፡ ታዲያ ለሩሲያ ለመዋጋት መሰለፋቸው ያለው አደጋ እጅጉን ያነሰ ነው ለህም ነው አያስገርምም የምለው፡፡
በአሁኑ ሰዐት በኢትዮጲያ ካለው ኑሮ ውድነት አኳያ የተሻለውን ምርጫ
እንደመረጡ አያጠራጥርም ሰው እንኳን ተከፍሎት እና የተሸለ ተስፋን ሰንቆ ቀርቶ የእናት ሀገር ጥሪ ተብሎ ከወንድሙ ጋር ሊዋጋም
ሆ ብሎ መነሳቱ የቅርብ ግዜ ትውስታ ነው ፡፡ ካዛም አልፎ በ መዲናዋ ነዋሪ ላይ እየተደረገ ያለው መገፋት የኑሮ ውድነት እና ሌሎች
ሌሎች ምክንያቶች አማረውት ሲጮህ ሰሚ ያጣ ማህበረሰብ ማምሻውን ከ ሩሲያ ኤምባሲ የሰማው መረጃ መርዶ እንደሚሆንበት ምንም ጥርጥር
የለውም ፡፡
በአሁኑ ሰአት በ መዲናችን አዲስ አበባ ከ አምስት ሚሊየን በላይ ህዝብ
እእደሚኖር መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው ፡፡ ምንያህሉ ስራ አለው ምን ያህሉስ መሰረታዊ ፈላጎቶቹ ተሟልተውልታል፡፡ በሁላችንም ልብ ውስጥ
መልሱን ያዘለ ጥያቄ ፡፡መጠለያ ፣ልብስ እንዲሁም ምግብ መሟላት ያለባቸው እንዲሁም ለሰው ልጅ መሰረታዊ ፈላጎቶች መሆናቸውን ተምሮ
ያደገ ማህበረሰብ ፡፡ አድጎ ተመርቆ ስራ ፈልጎ እድለኛ ከሆነ እና ስራ ካገኘ በውሃላ የሚከፈለው ደሞዝ በ አበዛኛው የስራ ማስታወቂያ
ላይ እንደምንመለከተው አራት ሺ ብር አይሞላም በዚህ አራት ሺብር እንደው እድለኛ ከሆነ እና ካጋጠመው 2500 ቤት ቢከራይ በ አንድ
ሺ አምስት መቶ ብር ከወር እስከ ወር ለመድረስ አስማት ሊያስፈልገው ነው ማለት ነው፡፡
ታዲያ ከመሰረታዊ ፈላጎቶች አንዱን እንኳን ለህዝቧ ማሟላት ያልቻለች
ሀገር ህዝቧን ኑሮ ከተወደደብህ ሙዝ በዳቦ ብላ ብሎ የሚመክር መንግስት ታቅፋ እንዴት እራሱን ለ ጦርነት የማይማግድ ህብረተሰብ
ማፍራት ትችልለች፡፡
ቧልት መሆኑን እያወቅን እንኳን እንደ እውነት ብንወስደው እና አንድ
ሰው ሙዝ በዳቦ እየበላ መኖር የሚችልበትን መንገድ ብናሰላ፤ አንድ ኪሎ ሙዝ አርባ ብር ገዝቶ ሁለት ዳቦ አስር ብር ቢገዛ እና
ምሳውን እንኳን ቢበላ በወር ለምሳ ብቻ አንድ ሺ አምት መቶ ብር ያስፈልገዋል፡፡ ታዲያ እንዴት ነው ቁርሱ ይቅር እና እራት ሳይበላ ታክሲ ሳይጠቀም ለንጽኅና
መጠበቂያው ሳሙና እና አንዳንድ አስፈላጊ ነገሮችን ሳይገዛ የሚኖረው
፡፡
ለዚህ ነው ለሩሲያ ተዋግቶ ህልሙን ቢያሳካ ተመራጭ መሆኑ የማያጠያይቀው
ወይ ያልፍለታል ወይ ያልፍበታል፡፡ ካለፈለት ከራሱ አልፎ ቤት መስራት ተአምር በሆነባት አዲስ አበባ ለቤተሰቡ ቤት ሰርቶ ጥሩ ኑሮ
ያኖራቸዋል፡፡ ካለፈበትም እዚህ በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በኑሮ ከሚደርስበት መገለል እና መገፋት አንደኛውን ይገላገላል፡፡ ድግሞ
ጦርነቱን ሩሲያ የምታሸንፍበት አጋጣሚ የሰፋ ነው ፡፡ እንኳን ተዋግቶ ሰው ከኑሮ በረከሰባት ሀገር ኢትዮጲያ ስንቱ አይደል በታጠቁ እና ለማህበረሰባችን እንዋጋለን በሚሉ ሀይሎች ብቻ የሚረግፈው፡፡
ሀገሬው
ቀን እስኪያልፍ ለ አባቴ ባሪያ ገረድ ያርገኝ የሚል ጥሩ አባባል አለው ቀን እስኪያልፍ ችግርችን ሁሉ ዝቅ ብሎ ማሳለፍ የለመደው ኩሩው ኢትዮጲያዊ በአሁኑ ሰአት በሀገራችን በ ፖለቲካውም
ይሁን በ ማህበራዊ ህይወቱ እንዲሁም በኢኮኖሚው ላይ ተፈጠረውን ክፉ ችግር ለማለፍ ዝቅ ቢል ክፋቱ ምን ላይ ነው፡፡
ከላይ
አንድ ደሞዝተኛ ኑሮውን እንዴት መግፋት እንደሚከብደው አሳይቻለው አሁን ደግሞ ስራ የሌለው አንድ ግለሰብ ኑሮውን በምን መንገድ
ሊመራው እንደሚችል ለናነተው መልሱን ልተወው፡፡ በዚ ላይ ደግሞ የህይወቱን ከሰባ አምስት በመቶ በላይ በትምህርት አሳልፎ በተማረበት
ፊልድ ስራ ማጣቱ ያማረረው ወጣት ሲጨመርበት የሁኔታውን ክብደት ያገዝፈዋል
፡፡
ተስፋ የጣለበት መንግስትም ቢሆን ሀገሬው በድርቅ ተሰቃይቶ የዝናብ
ያለ እያለ ከብቶች ሲያልቁበት እና ስጋው ተመናምኖ አጥንቱ አደባባይ ሲወጣ ዝም ብሎ እግዜሩ በምህረቱ የላከለትን ዝናብ እኔ ነኝ
እያለ ከማይጋፉት ፈጣሪ ጋር ከመጋፋት ይልቅ የረባ ነገር ሲያደርግ አይስተዋልም ፡፡ በየአመቱ ባስገነባዋቸው ዘመናዊ ከፍተኛ የትምህርት
ተቋማቶቼ ውስጥ ይህን ያህል ተማሪ አስመረኩ እንጂ ይህን ያህል የስራ እድል ፈጠርኩ ሲልም ተሰምቶ አያውቅም፡፡
ይልቁኑስ ህዝቤ ኑሮው ከ አቅሙ በለይ ሲሆን ሊስትሮም ሰርቶ ይሁን
ደፋ ቀና ብሎ እራሱን አቋቁሞ ሲኖር እኔ ባመቻቸውት የለውጥ ጎዳና ይህን ያህል ሰው ከድህነት ወደ መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ተሸጋገረ
እያለ ደረቱን ከመምታት ይልቅ ምንም ሲያደርግ አይስተዋልም ስለዚ አንዳንዴ እንዲበላ መንገድ ባንከፍትለት እንኳን ያገኘውን አጋጣሚ
እንዲጠቀም ዝም ብንለው የተሻለ ይመስለኛል፡፡
እንደውም ቢቻል ቢቻል እንዲህ አየነቱን አጋጣሚ መንግስት እራሱ ቢያመቻቸው
የሚያስመሰግነው ተግባር ስለመሆኑ ቅንጣት ጥርጥር አይኖረኝም፡፡ ህዝብ ብሶቱን ሲያሰማ ከማሰርም ችግርህ ምንድነው ብሎ ወርዶ መጠየቅ
ተገቢ ነው ችግሩን ሰምቶ ማሳለቅን ሳይጨምር፡፡
ይህ ጽሑፍ ሙሉ በሙሉ የፀሐፊው አመለካከት ሲሆን ኦርጂን ሳይጨምር
ሳይቀንስ እንደወረደ አቀርቦታል ፣ ማንኛውም አካል በፅሁፋቸው ላይ ምላሽ እንዲሰጥ መድረኩ ክፍት መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

አስተያየት ይለጥፉ