አዲስ የተመሠረተው የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሄደ



አዲስ አበባ፡- አዲስ የተመሠረተው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ትናንት አካሂዷል።

በስብሰባውም የፓርቲው ጉባዔ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በሚተገበሩበት ሁኔታ ላይ መክሯል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው የጉባዔው ውሳኔዎች ተግባራዊ የሚሆኑበት እቅድ ተዘጋጅቶ ውሳኔዎቹና አቅጣጫዎቹ በፍጥነት መተግበር እንዲጀምሩ ውሳኔ ማስተላለፉን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኮሚቴው በተጨማሪም አዲስ የተገነባውን የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የተመረቀ ሲሆን÷በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችንም መጎብኘቱ ታውቋል።

Post a Comment

አዲስ የድሮ