የሩሲያ ጦር የኬርሰን ክልልን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኦርጂን) በዩክሬን እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ የሩሲያ ጦር የኬርሰን ክልልን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ኢጎር ኮናሼንኮቭ እንዳሉት የዶኔስክ ህዝቦች ወታደሮች የማጥቃት ዘመቻቸውን አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን የዩክሬንን ፀረ ማጥቃት ሰብረው በመግባት በኬርሰን ክልል ውስጥ የምትገኘዋን ፓንቴሎሞኖቫካን መቆጣጠራቸውን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የዩክሬን የውጭ ቅጥረኛ ወታደሮችን ምሽግ መቆጣጠሩን 10 አሜሪካ ሰራሽ የጃቬሊን ፀረ ታንክ ሚሳኤል መያዙን ገልፀዋል።

በሩሲያ ኃይሎች የተያዙት ሁሉም የውጭ ጦር መሳሪያዎች ለሉሃንስክ እና ዶኔስክ ህዝቦች ህዝባዊ ሃይሎች እየተላለፉ መሆኑንም አስረድተዋል።

ባለፉት ቀናት በተካሄደው ዘመቻ የሩሲያ አየር ሀይል በተመረጡ 16 ኢላማዎች ላይ የተሳካ ድብደባ ያካሄደ ሲሆን የዩክሬንን ሱ 24 እና ሱ-25፣13 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እንዲሁም አንድ ሚግ 8 አውሮፐላን መምታት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ከተጀመረ ጀምሮ የሩሲያ ጦር በድምሩ 156 ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ 1 ሺህ 306 ታንኮች እና ሌሎች የጦር ተሽከርካሪዎችን፣ 127 ሮኬቶች፣ 471 የመስክ መድፍ ጠመንጃዎች እና ሞርታሮች ማውደሙንን ቃል አቀባዩ የገለጹት፡፡

የሩሲያ ባለስልጣናት 20 ቀናትን ያስቆጠረው ወታደራዊ ዘመቻ በተያዘለት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው ሲሉ መናገራቸውን የዘገበው ስፑትኒክ ነው።

ኦርጂን በቴሌግራም ይቀላቀሉን ፤

Post a Comment

አዲስ የድሮ