አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኦርጂን)በሁለት ዙር በተሰጠው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከተመዘገበው ውጤት 623 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በመጀመሪያው ዙር ፈተና የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 563 ሲሆን÷ በሁለተኛው ዙር የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደግሞ 623 መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
ከፍተኛ ውጤቱም በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ የተመዘገበ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ፈተናው በመጀመሪያው ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 600፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ 500 የተያዘ ሲሆን÷ በሁለተኛ ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 600 መያዙ ታውቋል።
አጠቃላይ ፈተናውን በሁለት ዙር 598ሺህ 679 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን÷ ከዚህም ውስጥ 287ሺህ 223 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።
አስተያየት ይለጥፉ