አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኦርጂን) ለ18ኛ ጊዜ በሚካሄደው የሰርቢያ-ቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና
ለሚሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ ምሽት አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።
በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መሥፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ተገኝተዋል።
አምባሳደር መሥፍን ቸርነት እና ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ÷ለልዑካን ቡድኑ አባላት የሥራ መመሪያና የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአሰልጠኞችና የአትሌቶች ተወካዮችም ስለዝግጅታቸው አስተያየት የሰጡ ሲሆን÷ የሰንደቅ ዓላማ ርክክብ መደረጉንም ከአትሌቲከክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አስተያየት ይለጥፉ