ገቢን ከማሳደግ አንጻር በቱሪዝም እና ማዕድን ዘርፍ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን የማጎልበት ተግባር እንደሚጠናከር ገልጸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በወቅታዊ ጉዳይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ የህዝብ ይሁንታ አግኝቶ መንግስትን እንዲመራ የተመረጠው የብልፅግና ፓርቲ የክልሉ አባላትን እና አመራር የመገምገም ስራ ተከናውኗል።
በቀጣይም አባሉንና አመራሩን የማጥራት ስራ ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ተቋማትንም የመፈተሽ ሰራ እንደሚከናወን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በተለይ ሰላምና ጸጥታን ከማጎልበት አንጻር የጸጥታ ሃይሉ ከአድሎ ነጻ ሆኖ ለሁሉም ነዋሪ እኩል የፍትህ አገልግሎት እንዲሰጥ የተጀመሩ ስራዎችን የማጠናከሩ ተግባርም እንደሚቀጥል አስረድተዋል።
የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ያሉት አቶ ኦርዲን፤ በቀጣይ ችግሮቹን በመፈተሽ አቅርቦትን የማሻሻል፣ ህገ ወጥ ንግድን የመከላከል እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።
የወጣቶችን የስራ እድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከብድር፣ከማምረቻ እና መሸጫ ቦታ ጋር በተያያዘ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት በተቀናጀ መልኩ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
”በክልሉ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለማቃለል ሁሉም አካል በርብርብ ይሰራል” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በተለይ በመንግስት ተቋም ውስጥ በትውውቅና በብሔር የሚሰራበት ሁኔታን በማስቀረት ፍትሃዊ የሆነ አሰራር እንደሚዘረጋ ተናግረዋል።
”በክልሉ ከመሬትና ከግዢ ጋር በተያያዘ ስርቆት፣ሌብነት እና ብልሹ አሰራር ይታያል፤ በቀጣይ ጠንከር ያለ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
በክልሉ በኢንቨስትመንት ስም ለበርካታ ዓመታት ተይዘው ያለማ መሬትን ለሚያለሙ ባለሀብቶች የማስተላለፍ ስራ እንደሚከናወንም አስታውቀዋል።
በክልሉ በፕሮጀክት ግንባታ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ስርዓት ለማሲያዝ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በክልሉ ገቢን ከማሳደግ አንጻር በቱሪዝምና ማዕድን ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን የማጎልበት ተግባር ለማጠናከር ትኩረት መሰጠቱን የገለጹት አቶ ኦርዲን፤ በክልሉ በሁሉም ዘርፎች ለሚከናወኑ ተግባራት ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቀርበዋል።
አስተያየት ይለጥፉ