የሀገር ውስጥ ዜና
አዲስ አበባ ፳፭ ቀን ሚያዚያ ፳፼፲፬ ዓ.ም (ኦርጂን)
የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጅፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ከሩሲያው አቻቸው ፕሬዚዳንት ብላድሚር ፑቲን ጋር በዚህ ሳምንት በቱርክ ሊገናኙ መሆኑ ተሰማ፡፡
መሪዎቹ በቱርክ ተገናኝተው በወቅታዊና የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃሉ።
በሩሲያ- ዩክሬን ያለውን ውጥረት ለማርገብ የሚያግዝ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ በሚቻልበት አግባብ ላይ እንደሚመክሩም ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡
በቱርክ ኢስታንቡል በፈረንጆች መጋቢት 29 በሩሲያ እና በዩክሬን ልዑካን መካከል ተደርጎ የነበረው ውይይት ጦርነቱን ለማስቆም በተደረገው የድርድር ሂደት ውስጥ እንደ ትልቅ ስኬት ይቆጠራል።

አስተያየት ይለጥፉ