የሰላም ሚኒስቴር ያስጀመረው የበጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ ልማት የት ደረሰ?

 የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ አበባ ፳፭ ቀን ሚያዚያ ፳፼፲፬ ዓ.ም (ኦርጂን)

ወጣቶች በሠለጠኑበት ሙያና ፍላጎት ባሳዩባቸው ዘርፎች ከተወለዱበት አካባቢ ርቀው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አገልግሎት እንደሚሰጡ የሰላም ሚኒስቴር አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ለዚህም 100 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች መመዝገባቸው፣ ነገር ግን ለመጀመርያ ዙር አሥር ሺሕ ወጣቶች መመልመላቸውና የመጀመርያ ዙር ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ ልማት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በተለያዩ ክልሎች የበጎ አድራት ሥራ መሥራታቸው ይታወቃል፡፡

እነዚህ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የሕይወት ክህሎትን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች 45 ቀናት ያህል ተሰጥቷቸዋል፡፡

ከደቡብ ጎንደር አካባቢ ተወላጅ እንደሆነች የምትናገረው ወጣት እመቤት  ሥልጠና ካገኙትና በመጀመርያ ዙር የበጎ ፈቃደኛ አገልጋይ ከሆኑት መካከል ናት፡፡

ደብረ ታቦር ላይ ተመልምለው ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ 45 ቀናት የተለያዩ ሥልጠናዎች እንደወሰዱ ወጣት እመቤት ትገልጻለች፡፡

ከሥልጠናው በኋላ አፋ ክልል ዞን አራት አልዋን ወረዳ የበጎ ፈቃድ ተግባር ለመሥራት እንደተመደበችና የበጎ ተግባር ሥራዋን እየሠራች እያለች የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወደ ወረዳው በመድረሱ፣ ከጓደኞቿ ጋር ተከራይታ የምትኖርበት ቤት ሙሉ በሙሉ በጦርነቱ መውደሙን፣ በጨለማ ከጓደኞቿ ጋር ጦርነቱን ሸሽተው ወደ ማያውቁት አካባቢ መጓዛቸውን ታስታውሳለች፡፡

ለተከታታይ አራት ወራት ቤተሰቦቿ የት እንዳለች እንደማያውቁ፣ ሕይወቷ አልፏል በማለት ተስፋ ቆርጠው እንደነበር፣ ለአራት ተከታታይ ቀናት ምግብ ሳያገኙ እንደቆዩ፣ በማያውቁት በረሃ ላይ ብዙ ተሰቃይተው እንደነበር ነግራናለች፡፡  

ወጣት እመቤት እንደተናገረችው፣ በሴትነታቸው ብዙ ፈተናዎችን አልፈዋል፡፡ በየመንገዱ ብዙ አሰቃቂ ነገሮችን ዓይተዋል፡፡ ጦርነቱን ሽሽት ሲጓዙ ብዙዎቹ ወንዶች በመሆናቸው እንቅልፍ አጥተው ከርመዋል፡፡ በእግር ሲጓዙ በመድከማቸውም እሷና ጓደኛዋ ወደ ኋላ ቀርተው ነበር፡፡

በእግራቸውና በባለ ሦስት እግር ሟጓጓዣ የተወሰኑ መንገዶችን እንደተጓዙ፣ ከዚያም በወልዲያ ከተማ ለሁለት ወራት መቆየታቸውን ታስታውሳለች፡፡

ከአፋር ክልል ጦርነት ሽሽት ሐምሌ 9 ቀን 2013 .. ተነስተው ከወር በኋላ ወልዲያ ከተማ መድረሳቸውን፣ ጥቅምት 14 ቀን 2014 .. ተመልሰው ሰመራ ከተማ መግባታቸውን ትገልጻለች፡፡

በብዙ ፈተናና ችግር ተፈትነው ቢያሳልፉም፣ በመንግሥት የተደረገላቸው ዕገዛ እንደሌለ፣ብትቸገሩ፣ ብትታመሙና አደጋ ቢደርስባችሁ ከጎናችሁ ነንሲሉ የነበሩ የመንግሥት አካላት በጭንቀታቸው ጊዜ ምንም ዕገዛ እንዳላደረጉላቸው ዕንባ በተሞላው ድምፀቷ በምሬት ተናግራለች፡፡

ከደቡብ ጎንደር ሲነሱ ማኅበረሰቡን በበጎ ፈቃደኝነት ለማገልገል መሆኑን፣ ቋንቋውና ባህሉ እንግዳ በሆነባት ቦታ ማኅበረሰቡን መስለው ሲኖሩ እንደነበር፣ ነገር ግን ከዚያ ጉድ ከተረፉ በኋላ እንኳን ለሞራላቸው የሥነ ልቦና ሕክምናና መሰል ዕገዛዎች እንዳላገኙ አክላለች፡፡  

የጦርነቱን አሰቃቂነትና መጥፎነት አምርራ የተናገረችው እመቤት፣ በወቅቱ ሴት መሆኗን እስክትጠላ ድረስ የተፈተነችበት መሆኑን፣ ቤተሰበቿ የሥራ ዕድል እንደምታገኝና እንደምትረዳቸው በሙሉ ልብ እርግጠኛ ሆነው እንደነበር፣ ይህ ባለመሆኑ መልሳ ወደ ተወለደችበት አካባቢ ስትመለስየሥራ ቅጥሩስእያሉ እየጠየቋት እንደሆነ በማዘን ጠቁማለች፡፡

ሰላም ሚኒስቴር ደውለው የተገባላቸው ቃል ምን ላይ እንደደረሰ ቢጠይቁም፣ጠብቁ ሥራ ትመደባላችሁእንደተባሉ ተናግራለች፡፡

ጋምቤላ ክልል አሶሳ ከተማ የደረሰው ወጣት ዓባይነህ ሥዩም፣ ‹‹ሰላም ሚኒስቴር መጀመርያ የገባልን ቃልና አሁን ያለንበት ሁኔታ ተፋልሶብናል፤›› ይላል፡፡

ለተከታታይ 45 ቀናት ሥልጠና ሲወስዱ፣ ጋምቤላ ክልል ለአሥር ወራት በበጎ ፈቃድ ካገለገሉ በኋላ በተመረቁበት ሙያ ሥራ እንደሚገቡ ተነግሯቸው ነበር፡፡ የዶርምና የምግብ እንደሚሸፈንላቸው ቃል መገባቱን፣ 3,276 ብር በወር ይከፈላቸው እንደነበርም ተናግሯል፡፡

ከአዊ ዞን ቲለሊ ከተማ ጋጉሳ ሽቡዳድ ለበጎ አድራጎት ሥራ ዕድሉን እንዳገኘ፣ ከዞን ጀምሮ ከአሥር ወራት በኋላ ሥራ እንደሚያገኙ እንደተነገራቸው፣ ከዚህ አካባቢ ለመጀመርያ ዙር የበጎ አድራጎት ሥራ የተመረጡትም 24 መሆናቸውን አስታውሷል፡፡

የኤሌክትሪካል ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ ትምህርቱን ማጠናቀቁን፣ ከበጎ አድራጎት ሥራው በኋላ ሥራ እንደሚያገኝ ተስፋ አድርጎ እንደነበር ጠቁሟል፡፡

ያነጋገርናቸው ወጣቶች እንደነገሩን፣ በሄዱ በመጀመርያ ሳምንት ማኅበረሰቡየመንግሥት ሰላዮች ሳይሆኑ አይቀሩምበማለት በጥርጣሬ ያያቸው ነበር፡፡ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በሶማሌና በሌሎች ክልሎች ላይ የደረሳቸው ወጣቶች በመጀመርያዎቹ ሳምንታት የማኅበረሰቡ ተቀባይነት ያላገኙ ቢሆንም በጊዜ ሒደት ተላምደዋል፡፡

አፋር ክልል ከደረሳቸው አንዱ ወጣት አየነው ክንዴ 270 በላይ ወጣቶች መሄዳቸውን፣ ከእነዚህ አገልግሎቱን ጥለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ መኖራቸውን አክሏል፡፡

 እነዚህ ወጣቶች እንደገለጹት፣ ከወረዳ እስከ ሚኒስቴሩ ድረስ ከበጎ ፈቃድ ሥራቸው በኋላ ሥራ እንደሚመደቡ ቃል ቢገባላቸውም፣ እስካሁን ተፈጻሚ አልሆነም፡፡

ለተከታታይ 45 ቀናት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ሥልጠና ወስደው ለአሥር በተከታታይ ወራት በየክልሎቹ በበጎ ሥራ ላይ አገልግለው ወደ አካባቢያቸው ከተመለሱ አራት ወራት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በስልክና በአካል የሥራ ሁኔታቸው ምን ላይ እንደደረሰ ቢጠይቁም፣ቆዩ ትዕግሥት ይኑራችሁተብለዋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ጀማል እንደተናገሩት፣ የፕሮግራሙ ዓላማ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ሲሆን፣ በጎ ፈቃድ ደግሞ ተከፍሎ ሳይሆን በግለሰብ ፈቃደኝነት በነፃ የሚደረግ አገልግሎት ነው፡፡

ሰላም ሚኒስቴር የበጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎትን ቀርፆ ለተግባር ሲነሳ፣ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኒክ፣ የሙያና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መለየቱንም አስረድተዋል፡፡

በዚህም 100,000 በላይ መለየታቸውን፣ እነዚህም ከትምህርት ክፍል ተመርቀው ሥራ ላይ ያልሆኑ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የመጀመርያ ዙር በጎ ፈቃደኞች ከሰብዕናና ከአመለካከት ጋር ተያይዞ፣ የሥራ ባህልና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ማግኘታቸውን፣ ከሥልጠናው በኋላ እንደ አገር ይጠቅማል የተባለው፣ ከመኖሪያ አካባቢያቸው ርቀው ከሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር መኖር እንዲችሉ ለማድረግ መሠራቱን ጠቁመዋል፡፡

ወንድም ወንድሙን ቢያውቀው ብዙ ችግር እንደሚቀርፍና ለአገር ግንባታ ሥራ አስተወጽኦ ስለሚኖረው የሥልጠና ሒደቱ ላይ አንዱ አንዱን እንዲያውቀው ዕድል መፍጠሩን፣ ከሥልጠና በኋላ ከመጡበት አካባቢ ርቀው ነፃ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጋቸውን፣ በዚህም ባሉበት አካባቢ ለሳሙናና ለአንዳንድ ወጪዎች የኪስ ገንዘብ ይሰጣቸው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የመጀመርያው ዙር በጎ ፈቃደኞች 10 ወራት ማገልገላቸውን፣ ፕሮግራሙም መስጠትን፣ መልመድን፣ ችግሮችን መጋፈጥና ለራስና ለአገር መቆምን ታሳቢ ያደረገ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

‹‹ሥልጠናውን ስታጠናቅቁ በተማራችሁበት ሙያ ትቀጠራላችሁ የሚባለው እሳቤ ትክክል አይደለም፡፡ ከፕሮግራሙ ስያሜ ቢታይ እንኳን ስለበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንጂ ስለሥራ ቅጥር የሚያወራ አይደለም፤›› ብለዋል፡

አሁንም ሁለተኛና ሦስተኛ ዙር በጎ ፈቃደኞች በተለያዩ አካባቢዎች እያገለገሉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

ትልቁ ችግር የነበረው ከምልመላው ጀምሮ የነበሩ ክፍተቶች መሆናቸውን፣ በጎ ፈቃደኞቹ ከወረዳ ጀምሮ ትክክኛ ያልሆነ መረጃ ተሰጥቷቸው ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ፡፡

ማኅበረሰቡን ማገልገል የተቋም ግዴታ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጎች ግዴታ መሆን እንዳለበት ያስረዱት አቶ ደረጄ፣ ወደፊት በሁሉም አካባቢ እንደሚተገበር ተናግረዋል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር አማካይነት አሁንም ብዙ ወጣቶች ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንደሚሄዱ፣ ነገር ግን ከሥራ ቅጥር ጋር የሚያያዝ ነገር እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ዜጋ ማኅበረሰቡን የማገልገል፣ የማወቅና፣ የመረዳዳት ኃላፊነት እንዳለበት ይህንንም በወጣቶች ለማስረፅ ያለመ ፕሮግራም እንደሆነና ቀጣይነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡    


ይህን ተጭነው በቴሌግራም ገጻችን ይቀላቀሉን





Post a Comment

አዲስ የድሮ