በመዲናዋ 10 ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶችን በአጭር ጊዜ በማጠናነቀቅ ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ እየተሰራ ነው

 


አዲስ አበባ ፣ ፲፪ ቀን ሚያዝያ ፳፼፲፬ (ኦርጂን) 

 

በአዲስ አበባ 10 ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶችን ግንባታ በሁለት ዙር በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ እየተሰራ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።

በአዲስ አበባ የነዋሪው ህዝብ ቁጥሩ እያሻቀበ በመምጣቱ የመኖሪያ ቤት እጥረት በስፋት እየተስተዋለ ሲሆን ይህን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል በመንግስት በኩል የተለያዩ የመፍትሄ ርምጃዎች እየተወሰዱ ነው።የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ሄኖስ ወርቁ፤ ከመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ቁጥር ጋር እጥረቱን ለማቃለል የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት 40/60 20/80 እና 10/90 የቤት ልማት ልማት ፕሮጀክት ሲከናወን መቆየቱን ጠቅሰው ከቤት ፈላጊው ብዛት አንፃር የፕሮጀክቶች ክንውን በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን ገልጸዋል።በዚህ ዓመትም በግንባታ ሂደት ላይ የነበሩ 68 ሺህ ቤቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለተጠቃሚ ቢተላለፉም ቀሪ 4 ሺህ ቤቶች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።   

በመሆኑም የመኖሪያ ቤት እጥረት ችግርን ለማቃለል ተጨማሪ የልማት ፕሮጀክት እየተከናወነ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸው በአዲስ አበባ 10 ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶችን ግንባታ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።በመጀመሪያው ዙር 5 ሺህ ቤቶችን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለተጠቃሚው ለማስተላለፍ ግንባታው እየተከናወነ መሆኑን ነው የገለጹት።

የመኖሪያ ቤት እጥረት ችግር በመንግስት ጥረት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ሌሎች አማራጮች አንዲኖሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።የውጭ ባለሃብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ ማድረግን ጨምሮ የግል አልሚ ባለሃብቱን ከማህበራት ጋር በማቆራኘት ለቤት ፍላጊዎች ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።የተገጣጣሚ ህንፃ ግንባታ ስራ በቴክኖሎጂ ታግዞ በአጭር ጊዜ ውስጥ የግንባታ ሂደቱን ማጠናቀቅ የሚቻልበት የቤት ልማት መርሐግብር መሆኑ ይታወቃል።

ይህን ተጭነው በቴሌግራም ይቀላቀሉን

 

Post a Comment

አዲስ የድሮ