ሀዋሳ፤ መጋቢት 8/ 2014 (ኦርጂን) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው በጉራጌ ዞን የተፋስስ እና የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን እየጎበኙ ነው።
ርዕሰ መስተዳድሩ በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ በተፋሰስ ልማት የተካሄዱ ስራዎችን በመጎብኘት በልማቱ ተሳታፊ አርሶ አደሮችን አበረታተዋል።
የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ መሐመድ ናስር በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት፤ በወረዳው ባለፉት ሁለት ወራት በተካሄደው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ከ38 ሺህ በላይ ህዝብ ተሳትፏል።
የወረዳው አርሶ አደሮችን ፥ወጣቶችንና የሴት አደረጃጀቶችን በማቀፍ በተካሄደው የተፋሰስ ልማት 5 ሺህ 460 ሄክታር መሬት መሸፈኑና ይህም ከእቅድ በላይ የተከናወነ ነው በማለት አስረድተዋል።
2 ሺህ 74 ኪሎ ሜትር የድንጋይ፥የአፈር እና የጠረጴዛ እርከን ስራዎች መከናወናቸውንም ጠቅሰዋል።
የተጎዳ 631 ሄክታር መሬትን ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ በመከለል እንክብካቤ እየተደረገለት እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ በወረዳው አቡሶጃ ቀበሌ በ120 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የበጋ ስንዴን እየጎበኙ ሲሆን ከቀበሌው አርሶ አደሮች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
በጉብኝቱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞኑ አስተዳደርና የግብርና ሴክተር የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
አስተያየት ይለጥፉ