ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችን ማሳ በመጎብኘት ላይ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበጋ መስኖ የለሙ የስንዴ ማሳዎችን እንደዚሁም የቡና ልማትን ነው በመጎብኘት ላይ የሚገኙት።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋርም በቀጠናው የዓለም ባንክ ዳይሬክተርና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በመስክ ጉብኝቱ ላይ ተገኝተዋል።
አስተያየት ይለጥፉ